የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ተስተካካይ ሦስት ጨዋታ ተደርገው አርባምንጭ ከተማ እና ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ሀዋሳ ከተማ እና ሀምበርቾ ነጥብ ተጋርተዋል።
ቀዳሚ በነበረው መርሃግብ ሀዋሳ ከተማ ከሀምበርቾ ከተማ ተገናኝተው ነጥብ ተጋርተዋል። ቀዝቃዛ የጨዋታ እንቅስቃሴ በታየው በረፋዱ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ በመጀመሪያ አጋማሽ የጨዋታ ብልጫ መውሰድ ችለው ነበር። ሆኖም ሳቢ ያልነበረው ጨዋታ እምብዛም የግብ ሙከራ አልታየበትም። አልፈው አልፈው ሀዋሳ ከተማ የሚያገኙትን ኳስ በደካማ አጨራረስ ሳይጠቀሙ ሲቀሩ ተስተውለዋል። ሀምበርቾ በአንፃሩ ግብ እንዳይቆጠርባቸው ወደኋላ አፈግፍገው ሲጫወቱ የነበሩ ሲሆን ጠንከራው ሀዋሳ ከተማ ግብ እንዳያስቆጥርባቸው እስከ ሀያ አምስተኛው ደቂቃ በመከላከል መቆየት ችለዋል።
በ25ኛው ደቂቃ ሀዋሳዎች በእርስ በርሰ ቅብብል ኳስ ይዘው በመግባት በመስመር በኩል የተሻገረውን ኳስ እሙሽ ዳንኤል አግንታ መረብ ላይ አሳርፋ ሀዋሳ ከተማ መሪ እንዲሆን ሆኗል። ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ሀዋሳዎች ወደጨዋታው በመመለስ ተጨመሪ ግብ ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርጉም ጨዋታው ሌላ ተጨመሪ ግብ ሳያስመለክት እረፍት ወጥተዋል።
ጨዋታው ከእረፍት ሲመለስ ልክ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ብዙም የግብ ሙከራ አልታየበትም። ሆኖም ግን ሀዋሳ ከተማ ግብ መሆን የሚችሉትን ያለቁ ኳሶችን አግንተው ሳይጠቀሙ ሲቀሩ ተስተውለዋል። ሀምበርቾ በአንፃሩ በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ ለመመለክት ትችሏል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ በዚህ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ በታየው ውስጥ ሀምበርቾዎች ኳስ ይዘው ወደሀዋሳ ከተማ ግብ ክልል መገቡበት ሰዓት ተከላካዮች ባደረጉት በእጅ ንክኪ ፍፁም ቅጣት ምት አግንተዋል። መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪው 5ኛ ደቂቃ ብርሃን ኋይለስላሴ ከመረብ ጋር አገናኝታ ጨዋታው ነጥብ በመጋራት ተጠናቋል።
ቀን ሰምንት ሰዐት አርባምንጭ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያገናኘው መርሃግብር በአርባምንጭ ከተማ በላይነት ተጠናቋል። በመጀመሪያው አጋማሽ ጠንከር ብለው የገቡት አርባምንጮች በርከት ያለ የግብ ሙከራ እና አስቆጪ የሚባሉ አጋጣሚዎችን አግኝተው መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንፃሩ ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴ በመጀመርያው አጋማሽ ያደረጉ ሲሆን አልፈው በሚያደርጉት መልሶ ማጥቃት ግብ ማስቆጠር የሚችሉበትን አጋጣሚ ቢፈጥሩም ለማስቆጠር ሲችገሩ ተስተውለዋል። የጨዋታ ብልጫ የወሰደው አርባምንጭ መምራት የሚችሉበትን ግብ ለማስቆጠር ሀያ ስድስት ደቂቃ መጠበቅ ግድ ሆኖባቸዋል። በ26ኛው ደቂቃ በንክክ የተገኘውን ኳስ ሠርከአዲስ ካሣዬ ከመረብ ጋር አገናኝታ በአርባምንጭ ከተማ መሪነት እረፍት ወጥተዋል።
ከመልበሻ ክፍል መልስ ሁለቱም ቡድኖች በመነቃቃት ኳስ ጠቆጣጥሮ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ክልል ሲገቡ ተስተውለዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የግ ማግባት ሙከራ በማደረግ የተሻሉ ቢሆንም አርባምንጭ ከተማዎች ነጥቡን በመከላከላተው ግብ ለማስቆጠር ተቸግረዋል። አርባምንጭ ከተማም ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር በመልሶ ማጥቃት የግብ ሙከራ አድርገዋል።ሆኖም ግን ሌላ ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠር ብቸኛ ግብ አርባምንጭ ከተማ በጠባብ ወጤት ሦስት ነጥብ አሳክቷል።
የእለቱ ተጠባባቂው ጨዋታ ቦሌ ክ/ከተማን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገናኝቶ ንግድ ባንክ በሰፊ ግብ ልዩነት አሸንፏል። በርካታ የግብ መግባት ሙከራ ከማራኪ እግር ኳስ አጨዋወት ጋር ባስመለከተው በዚህ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ተቆጣጥረው በጥንቃቄ ሲጫወቱ ተስተውለዋል። ቦሌ ክ/ከተማ ኳስን መስርተው ከተከላካይ መስመር ጀምረው ወደፊት እየሄዱ የግብ ሙከራ ሲያደርጉ ንግድ ባንክም በመለሶ ማጥቃት መድረሻቸውን ሴናፍ ዋቁማ ላይ ባደረጉ ኳሶች ሳቢ ጨዋታ አስመልክተዋል። ቶሎ ቶሎ ወደተቃራኒ ቡድን የገቡት ሁለቱም ቡድኖች ብዙ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አግንተው ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ሲጫወቱ ስለነበር ግብ ሳያስቆጥሩ አርባ ደቂቃዎች ተቆጥረዋል። በ40ኛው ደቂቃ ላይ ንግድ ባንኮች ኳስ ይዘው ወደግብ ክልል በገቡበት ቅፅበት የቦሌ ተከላካዮች ባደረጉት በእጅ ንክክ ፍፁም ቅጣት ምት አግንተዋል። ሴናፍ ዋቁማ በመምታት ከመረብ ጋር አገናኝታ ንግድ ባንክን መሪ አድርጋ ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ጨዋታው ከእረፍት ሲመለስ ንግድ ባንክ ጠንከር ብለው በመመለስ ገና ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ተጨማሪ ግብ በማስቆጠር መሪነታተውን አስፍተዋል። በ46ኛው ደቂቃ ጥሩ ስትንቀሳቀስ የነበረችው አርያት ኡዶንግ ከሰናይት ቦጋለ ጋር በአንድ ለአንድ ቅብብል በመግባት ኳስን መረብ ላይ አሳርፋ ንግድ ባንክ 2ለ0 እንዲመራ ሆኗል። ቦሌዎች ወደጨዋታው መመለስ ሚያስችላቸውን አጋጣሚዎች በመፍጠር ግብ ለማስቆጠር ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ጠንከራ ሆኖ የዋለውን የንግድ ባንክን ተከላካይ መሰመር አልፈው ግብ ማስቆጠር ተስኗቸዋል። በኳስ ቁጥጥር ጥሩ የነበሩት ንግድ ባንኮች በ75ኛው ደቂቃ መሪነታቸውን እና ጨዋታውን መጨረስ የቻሉበትን ኳስ ከመረብ ጋር አገናኝተዋል። በመለሶ ማጥቃት የተገቸውን ኳስ አርያት ኡዶንግ በመሰመር ላይ ሆና አክርራ ወደግብ የመታችው ኳስ ከመረብ ጋር ተገናኝቶ ጨዋታው 3ለ0 በሆነ ሰፈመ ግብ ልዩነት እንዲጠናቀቅ ሆኗል።