የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 20ኛው ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሲጀምር ነቀምቴ ከተማ ተጋጣሚውን አሸንፏል። ሀላባ ከተማ እና ስልጤ ወራቤ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል።
የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ነቀምቴ ከተማን ከሞጆ ከተማ አጋኝቶ ነቀምቴ ከተማ በመጀመሪያው አጋማሽ በምትኩ ማመጨ አማካኝነት ባስቆጠሩት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ አሳክቷል። ጥሩ የመጀመሪያ አጋማሽ ያሳለፈው ነቀምቴ ከተማን ያስመለከተው አንደኛው አርባአምስት ነቀምቴ ከተማ ተጋጣሚውን በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደበትና ረጃጅም ኳሶችን በመጣል ከባባባድ ሙከራዎችን ያደረጉበት ነበር። ሞጆ ከተማ በውጤት ቀውስ መግባቱን ተከትሎ በጨዋታ ብልጫ የተወረደበትን አጋማሽ ሲያሳልፍ እምብዛም ወደተቀራኒ ቡድን ግብ ክልል ኳስ ይዘው ሲገቡ አላስተዋልንም።
በርከት ያለ ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩት ነቀምቴዎች የጥረታች ውጤት የሆነቺዋን ግብ አስቆጥረዋል። በ16 ኛው ደቂቃ ተመስገን ዱባ ኳስ ይዞ በሚገባበት ወቅት የሞጆ ከተማው ተከላካይ መሳፍንት ነጋሽ ተመስገን ዱባ ላይ በሰራው ጥፋት አደገኛ ቦታ ላይ ቅጣት ምት አግንተዋል። ቅጣት ምቱን በግሩም ሁኔታ ምትኩ ማመጨ መረብ ላይ አሳርፏል። ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጫና መፍጠር ብችሉም ሌላ ግብ ሳያስመለክቱ የመጀመሪያው አጋማሽ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተገባዶ ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከመልበሻ ክፍል ጨዋታው ሲመለስ ሞጆ ከተማ ተደራጅተው ኳስ ሲጫወቱ ተስተውለዋል።በዚህም አቻ ለመሆን ኳስ መስረተው የዘው በመግባት ከባባድ ጥቃት ሰንዝረዋል። ነቀምቴ ከተማም ነጥባቸውን ለማስጠብቅ በጥሩ አደራደር ወደኋላ አፈግፍገው በመከላከሉ ረገዱ ስኬታማ የሆኑበትን ሁለተኛ አጋማሽ አሳልፈዋል። ብልጫ የወሰዱት ሞጆ ካለባቸው ውጤት ማጣት ለመውጣት በተደጋጋሚ የሚያደርጉትን የግብ ማግባት ጥቃት ጠንከራ ሆኖ የዋለው የነቀምቴ ከተማ ተከላካይ መስመር ኳሶችን ሲያፀዳ ተስተውለዋል።በዚህም መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ግዜ ተጠናቆ ተጨማሪ በታየው ላይ ካሳሁን ሃይለሚካኤል ብርሃኑ ደስታ ላይ በሰራው ከባድ ጥፋት ቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተ ሁለተኛ ተጫዋች ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በጎዶሎ ተጫዋች ቀሪውን የጨዋታ ክፍለጊዜ ለማሳለፍ ተገደዋል። ሞጆ ከተማ ጠንከር ያለ ሙከራ በማድረግ አቻ ሆኖ ለመጨረስ ጥረት ቢያደርግም ጨዋታው በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠር ብቸኛ ግብ ነቀምቴ ከተማን አሸናፊ በማድረግ ተገባዷል።
ሁለተኛው ጨዋታ ሀላባ ከተማን ከስልጤ ወራቤ አገናኝቶ ያለግብ ተጠናቋል።
ሀላባ ከተማ በኳስ ቁጥጥርም ሆኖ በግብ ማግባት ሙከራ ብልጫ በወሰዱበት በዚህ ጨዋታ በስልጤ ወራቤ ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈፀምባቸው ተስተውሏል። ስልጤ ወራቤም ረጃጅም ኳሶችን ከተከላካይ ጀርባ በመጣል በመልሶ ማጥቃት ሙከራ አድርጓል። አደገኛ ሙከራዎችን ያደረጉት ሀላባዎች በርከት ያለ አደገኛ ሙከራዎችን በመጀመሪያው አጋማሽ ቢያደርጉም በሁለተኛው ዙር ብዙም ቋም ተሳልፊ ሲሆን ያልተስተዋለው ግብ ጠባቂያቸው አደገኛ ሚባሉ ሙከራዎቸን አድኗል። አደገኛ ሚባለውን ሌላኛውን ሙከራ በ44ኛው ደቂቃ ላይ ከማል ሀጂ ያደረገ ሲሆን ከፀጋአብ ጋር አንድ ለአንድ ተቀባብለው የመታትን ኳስ ቋም ብረት የመለሰበት ኳስ ትታወሳለች። ሆኖም ግን ጨዋታው ግብ ሳያስመለክት የመጀመሪያ አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው ሲመለስ ጨዋታውም ግለቱን እየጨመረ ጥሩ የኳስ ቅብብል ከግብ ማግባት ሙከራዎች ጋር ለተመልካች አስመልክቷል። ቶሎ ቶሎ ኳሶችን በመቀባባል ሀላባ ከተማ ግብ ለማግባት ሙከራ ሲያደርግ ግብ መሆን ሚችሉ አጋጣሚዎችንም አግንተው በደካማ አጨራረስ ሲያመክኑ ተስተውለዋል። ስልጤ ወራቤም በአንፃሩ አልፈው አልፈው ይዘው የሚገቡትን አጋጣሚ አምክነዋል። ሀላባ ከተማ ባንዴ በርከት ያሉ የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ ልክ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ኳስን ቶሎ ቶሎ ይዞ በመግባት ሙከራ ሲያደርግ ስልጤ ወራቤም አንንዳንድ የተጫዋች ቅያሪ ማድረጉ ጨዋታው በአዲስ መልክ ጥሩ ፉክክር እንዲኖረው አድርጓል። እንዲህ እያለ ጨዋታው ግብ ሳይቆጠር ወደመገባደጃው ሲደርስ ሁለቱም ቡድኖች ያለቁ ኳሶችን አግንተው ሳይጠቀሙ ቀርተው ጨዋታው ያለግብ ተጠናቋል።