የሀገራችን እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዳኞች ኮሚቴነት ሲሰሩ የቆዩትን አባላት በመበተን ኮሚቴውን በአዲስ መልክ አዋቅሯል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በአልቢትር ኮሚቴነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዮ አባላትን በአዲስ መልክ በተሻሻለው መተዳደርያ ደንብ መሰረት መነሳታቸውን አውቀናል። በዚህ መነሻነት ሰብሳቢው ሸረፋ ዴሌቾን ጨምሮ አራት የኮሚቴው አባላት የተነሱ ሲሆን በምትካቸውም በቀጣይ ዓመትታት ኮሚቴውን በበላይነት እንዲመሩ በቅርቡ እራሳቸውን ከዳኝነት ያገለሉት የቀድሞ ኢንተርናሽናል አልቢትሮች ለሚ ንጉሴ፣ ክንዴ ሙሴ፣ ሊዲያ ታፈሰ፣ ሸዋንግዛው ተባበል እና ክንፈ ይልማ ኮሚቴውን እንዲመሩ መደባቸው ሲታወቅ የኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን ሸዋንግዛው ተባበል መመረጣቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከወራት በፊት በኮሚቴው ውስጥ በሙያቸው እገዛ እንዲያደርጉ ለሚ ንጉሴ፣ ሊዲያ ታፈሠ እና ክንዴ ሙሴ ተካተው የነበሩ ሲሆን አሁን በተዋቀረው ኮሚቴ ቋሚ ቦታ ማግኘታቸው ተሰምቷል።