ካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ አውደ ጥናት በአራት ሀገራት ለማካሄድ ሲወስን ኢትዮጵያም እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።
የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) 54 አባል ሀገራትን ያካተተ አውደጥናት ለማካሄድ ዝግጅቱን መጀመሩን ሲያሳውቅ በሞሪታኒያ በሚጀምረው አውደጥናቱ በተለያዩ አራት ሀገራትም እንደሚቀጥል ሲታወቅ ሀገራችን ኢትዮጵያም አዘጋጅ ሆና መመረጧ ታውቋል። በዚህም
– ከዛሬ ሚያዚያ 14 ጀምሮ እስከ ዓርብ ሚያዚያ 18 በሞሪታኒያ
– ከሚያዚያ 21 እስከ ሚያዚያ 25 በአልጄሪያ
– ከሚያዚያ 30 እስከ ግንቦት 4 በኢትዮጵያ
– ከግንቦት 11 እስከ ግንቦት 15 በጋና አዘጋጅነት እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል።
ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው አውደ ጥናት
ኢትዮጵያ
ኤርትራ
ሶማሊያ
ሲሼልስ
ዛምቢያ
ማላዊ
ናሚቢያ
ሞሪሽየስ
ዚምባቡዌ
ደቡብ ሱዳን
ሱዳን
ታንዛኒያ
ሊቢያ
ዩጋንዳ
ሩዋንዳ
ዛንዚባር ( ተጋባዥ እንግዳ )
የሚካፈሉ ይሆናል።