2024 የፊፋ ባጅ ያገኙ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እና አንድ ኢንስትራክተር ዛሬ ወደ ግብጽ ካይሮ ለስልጠና እንደሚያመሩ ታውቋል።
የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በ2014 ያቋቋመው ይህ የስልጠና መርሐግብር ለፊፋ ዳኞች በአዳዲስ የጨዋታ ሕጎች ላይ በቀጥታ ዕውቀትን ለመስጠት ያለመ ሲሆን በወንዶች 13 ዋና እና 19 ረዳት በሴቶች 8 ዋና እና 10 ረዳት ዳኞች በድምሩ 50 ዳኞች ፣ 4 ኢንስትራክተሮች ፣ አንድ IT Support እንዲሁም 3 የ ካፍ ስታፎች ከግንቦት 12-16/2016 በግብጽ ካይሮ በሚካሄደው የስልጠና መርሐግብር እንደሚሳተፉ ታውቋል።
በዚህም መሠረት ከሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ፣ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ ፣ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ አሸብር ታፈሰ እና ኢንስትራክተር ሊዲያ ታፈሰ ዛሬ ወደ ግብጽ ካይሮ እንደሚያቀኑ ታውቋል።