ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚደረጉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ26 ተጫዋች ጥሪ አቅርቧል።
ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ሀገራት በተለያዩ ምድቦች ተከፋፍለው የማጣሪያ ፍልሚያዎችን እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በኋላም የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች በቀናት ልዩነት ይከወናሉ። የሀገራችን ኢትዮጵያ አሰልጣኝ የሆኑት ገብረመድኅን ኃይሌም ከታች ለተዘረዘሩት 26 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
ግብ ጠባቂዎች
አቡበከር ኑራ – ኢትዮጵያ መድን
ሰዒድ ሀብታሙ – አዳማ ከተማ
ፍሬው ጌታሁን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ተከላካዮች
ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
ሄኖክ አዱኛ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያሬድ ባየህ – ባህር ዳር ከተማ
ፈቱዲን ጀማል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሚሊዮን ሰለሞን – ኢትዮጵያ መድን
ፍሬዘር ካሳ – ባህር ዳር ከተማ
ፍቅሩ ዓለማየሁ – አዳማ ከተማ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያሬድ ካሳዬ – ኢትዮጵያ መድን
አማካዮች
ቢኒያም ዐይተን – አዳማ ከነማ
ጋቶች ፓኖም – ፋሲል ከነማ
ወገኔ ገዛኸኝ – ኢትዮጵያ መድን
ብሩክ ማርቆስ – ሀዲያ ሆሳዕና
አብነት ደምሴ – ወላይታ ድቻ
አብዱልከሪም ወርቁ – ኢትዮጵያ ቡና
ፉዓድ ፈረጃ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቢኒያም በላይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አጥቂዎች
መስፍን ታፈሰ – ኢትዮጵያ ቡና
ሀብታሙ ታደሰ – ባህር ዳር ከተማ
ቸርነት ጉግሳ – ባህር ዳር ከተማ
ቢንያም ፍቅሬ – ወላይታ ድቻ
ከነዓን ማርክነህ – መቻል
ምንይሉ ወንድሙ – መቻል
* ብሔራዊ ቡድኑ ግንቦት 29 ከጊኒ ቢሳው ፣ ሰኔ 2 ደግሞ ከጅቡቲ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።