“ስለ አቡበከር ናስር ማውራት አልፈልግም”

ኢትዮጵያዊው ከብራዚላውያኑ ጋር ያለው እህል ውሃ ያበቃ ይመስላል…..

ከወራት በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናስር ለእግር ኳስ ሕይወቱ አደጋ የሆነ ጉዳት እንዳጋጠመው፤ ለማገገም በጣም እየታገለ እንዳለ እና በቅርቡ ይመለሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ በመግለፅ ክለቡ ይፋዊ መግለጫ ይሰጥበታል ያሉት የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሮላን ማክዌና በትናንትናው ዕለት ተጫዋቹን አስመልክተው  “Power Fm” ለተባለ የሬድዬ ጣቢያ  የሰጡት አስተያየት አነጋጋሪ ሆኗል።


አሰልጣኙ ስለ አቡበከር ናስር አሁናዊ ሁኔታ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ “እሱ የሰንዳውንስ ተጫዋች ስላልሆነ ስለ አቡበከር ናስር ማውራት አልፈልግም፤ ምክንያቱም በሰንዳውንስ ተጫዋችነት አልተመዘገበም።” የሚል ምላሽ ቢሰጡም ክለቡ በይፋ ያሳወቀው ነገር የለም።