ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ወደ ጋናው ክለብ ?

አሻንቲ ኮቶኮ ለአቡበከር ናስር የሙከራ ዕድል እንዳመቻቸ ጋና ሶከር ኔት ዘግቧል።

ከደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ያለውን ቆይታ በውል ያልታወቀው ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር ወደ ጋናው አሻንቴ ኮቶኮ ሊያቀና እንደሆነ ጋና ሶከር ኔት የተባለ ሚድያ ገልጿል። በጋና እግርኳስ ታማኝ ከሚባሉ መገናኛ ብዙሐን አንዱ የሆነው ይህ ተቋም ኢትዮጵያዊው አጥቂ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሙከራ ዕድል እንደተመቻቸለት እና በተሰጠው ጊዜ የቴክኒክ ቡድኑን የሚያሳምን ብቃት ካሳየ ቡድኑን የመቀላቀል ዕድል እንዳለውም ጠቅሷል።

ካለ ዋንጫ የውድድር ዓመቱን ያጠናቀቀውና ቡድኑን ለማጠናከር በርካታ ዝውውሮች ይፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ክለቡ በአንድ ሳምንት ውስጥ የአቡበከር ናስርን የሙከራ ዕድል ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደሆነም ተጠቅሷል።

የአቡበከር ናስርን የተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ በቀጣይ ቀናት ግን ጉዳዩን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።