​ቡናማዎቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል

አህጉራዊ ውድድር የሚጠብቀው ኢትዮጵያ ቡና የአጥቂ እና የተከላካይ አማካይ ሥፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት እና በኢትዮጵያ ዋንጫ ወላይታ ድቻን 2ለ1 በመርታት ቻምፒዮን የሆኑት ኢትዮጵያ ቡናዎች ኢትዮጵያን ወክለው በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በመሳተፍ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያቸውን ከኬንያ ፖሊስ ጋር የሚያደርጉ ሲሆን ስብሰባቸውን ለማጠናከር ደግሞ ቀደም ብለው ወደ ዝውውር ገብተው ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች እስራኤል ሻጎሌ ነው። በአርባምንጭ ከተማ እና ነገሌ አርሲ ተጫውቶ ያሳለፈው አጥቂው በ2016 የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ለባቱ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ማረፊያው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።

ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ኦካይ ጁል ነው። በጉለሌ እና ለገጣፎ ለገዳዲ ተጫውቶ ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ በ2016 በከፍተኛ ሊጉ በሀላባ ከተማ ቆይታ አድርጎ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።