ቡሩንዲያዊው ተጫዋች ቡናማዎቹን ለመቀላቀል ተስማማ

የብሩንዲ ዜግነት ያለውን የመስመር አጥቂ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ስምምነት ፈፅሟል።

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተጨማሪ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ከፊት የሚጠብቀው ኢትዮጵያ ቡና እስከ አሁን ወደ ክለቡ ሦስት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ አንድ የጋና ዜግነት ያለውን ግብ ጠባቂን ከውጪ ሀገር ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ የብሩንዲ ዜግነት ያለውን የቀኝ መስመር ተጫዋቹ አልፍሬድ ኑኩሩንዚዛን ለማስፈረም ስምምነት ፈፅሟል።

በሀገሩ ክለብ ቡማሙር የከፍተኛ የግብ አስቆጣሪ ሆኖ በመፈፀሙ ወደ ግብፁ ክለብ አልተሀድ አሌክሳንድሪያ ከስምንት ወራት በፊት አምርቶ ቆይታን በማድረግ ከወራት በፊት በድጋሚ ተመልሶ በቡማሙር እንዲሁም ኤንጂል ኑዌር በተበላ ክለብ ቆይታን ይህ ተጫዋች ካደረገ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቷል።