ሙሉቀን አዲሱ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ማምሻውን ማረፊያው ወላይታ ድቻ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው ወላይታ ድቻ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ መሪነት በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ በመግባት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነውን ሙሉቀን አዲሱን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረማቸውን ከክለቡ እና ከተጫዋቹ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

የቀድሞው የነገሌ አርሲ ፣ ገላን ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ሙሉቀን አዲሱ በሲዳማ ቡና ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት ካሳለፈ በኋላ ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዓመታት አበባየው ሀጂሶን በተቃራኒው ወዳጡት የጦና ንቦቹ ማምሻውን ማምራቱ ተረጋግጧል።