ባንክ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቀ

ቻምፒዮኖቹ ወደ ዝውውር ገብተዋል

የወቅቱ የሊጉ ቻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አገባደደ። ቢኒያም ካሳሁን እና አብዱልከሪም መሐመድ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነዋል።


ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያሳለፈው የቀድሞ የደቡብ ፓሊስ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ የመስመር ተከላካይ ቡድኑ በአምበልነትም ጭምር ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ቻምፒዮኖቹ አምርቷል። ሌላው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዓመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ውጤታማ ዓመት አሳልፎ የቡድኑ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተሸለመው ቢኒያም ካሳሁን ነው። የኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ውጤት የሆነው ተጫዋቹ የእናት ክለቡን ቡናን ዋናው ቡድን ጨምሮ በኢትዮጵያ መድን እና በኢትዮ ኤሌክትሪክ መጫወት የቻለ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲገቡ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። አሁን ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ዳግም ለመገናኘት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል።