በዩጋንዳ ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊው ወደ ሀገር ቤት ሊመጣ ነው

የወቅቱ የዩጋንዳ ፕሪሚየር ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊ የግብ ዘብ የሀገራችንን ክለብ ሊቀላቀል ነው።


ሳሙኤል ሳሊሶ እና አበባየሁ ሀጂሶን አስፈርመው የደስታ ደሙን ውል ያራዘሙት ሲዳማ ቡናዎች ዩጓንዳዊውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት በአስራ ሁለት ጨዋታዎች መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት የዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ ወርቅ ጓንት አሸናፊ የሆነው ቶም ኢካራ ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል የተስማማ ተጫዋች ሆኗል።


ቡድኑ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾ አንዱ የሆነው ይህ የሃያ ሰባት ዓመት ግብ ጠባቂ ከዚ በፊት ቡል፣ ዩጋንዳ ፖሊስ፣ ካምፓላ፣ ምባራራና ቡሶጋ ለተባሉ ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን በብሔራዊ ቡድን ደረጃም ለዋናው እና ለታዳጊ ቡድኑ መጫወት ችሏል። ተጫዋቹ በቀጣይ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎም ይጠበቃል።