አማኑኤል ዮሐንስ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ላለፉት አስርት ዓመታት ቡናማዎቹን ያገለገለው አማኑኤል ዮሐንስ ወደ ሌላ ክለብ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።

ገና በታዳጊነቱ አንስቶ ኢትዮጵያ ቡናን በመቀላቀል ያለፉትን አስር ዓመታት ከቡድኑ ጋር አብሮ መዝለቅ የቻለው አማካይ አማኑኤል ዮሐንስ ኢትዮጵያ ቡናን በአንበልነት ከማገልገሉ ባሻገር ሌላ ማልያ ለብሶ እንደማያቅ ይታወቃል። ተጫዋቹ ከቡናማዎቹ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ከቆየ በኋላ መዳረሻው ታውቋል።

አማኑኤልን ያስፈረመው ክለብ መቻል ነው። በትናንትናው ዕለት ዝውውሩን ተቀላቅሎ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም የተስማማው መቻል አማኑኤልን በሁለት ዓመት ውል ወደ ስብስቡ መቀላቀሉ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።