በተጫዋቾች ዝውውር መመርያ ዙርያ በሁለት ተቋማት እየተሰጠ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ የሊጉ ሰብሳቢ ምን አሉ?
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመወከል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም ከሊጉ አክስዮን ማኀበር ደግሞ ሰብሳቢው መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ እና ስራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ሰይፉ በአሁኑ ሰዓት በካፒታል ሆቴል በተጫዋቾች የዝውውር መመርያን በምን ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጋዜጣዎ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።
በዚህ መግለጫ ላይ ጠንከር ያለ ንግግር ያደረጉት የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዝደንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ “ክለቦች የበጀት መመሪያው ሲወጣ አጨብጭበው ነበር ሁሉም ተቀብለው ነው የወጡት። አሁን የምንሰማው እየደረሰን ያለ ጭምጭምታ ግን መመርያውን በመተላለፍ ተቃራኒው ዝውውሩ እየተፈፀመ እንደሚገኝ ነው። የምንሰማው ጭምጭምታ እውነት ሆኖ ከተገኘ ወይ ህጉ ይከበራል አልያም ሊጉ ይፈርሳል።” በማለት ሊግ ካምፓኒው የያዘውን አቋም አንፀባርቀዋል። አጠቃላይ የጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃላይ ሀሳቦችን በቀጣይ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።