አርባምንጭ ከተማ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

አዲስ አዳጊው አርባምንጭ ከተማ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም የተመለሰው እና በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተካፋይ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ከቡድኑ አሠልጣኝ ጋር ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንደሚቆይ የተረጋገጠ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ የነበሩ እና ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛው ሊግ ዕርከን ካሳደጉ ተጫዋቾች መካከል የሦስቱን አድሶላቸዋል።

ከጅማ አባጅፋር በኋላ በአርባምንጭ መለያ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ያሳለፈው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አካሉ አትሞ ውሉ የተራዘመለት ሲሆን በሀምበርቾ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ የተጫወተው የመስመር ተከላካዩ ሳሙኤል አስፈሪ እንዲሁም ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘው ሌላኛው የመስመር አጥቂ በፍቅር ግዛቸው ውላቸው በቡድኑ አራዝመዋል።