ወላይታ ድቻ የክረምቱ አራተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

የጦና ንቦቹ ከአዲስ አዳጊው ክለብ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሳቸውን አጠናክረው ለመቅረብ ይረዳቸው ዘንድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሙሉቀን አዲሱን ፣ ቴዎድሮስ ታፈሰ እና ውብሸት ክፍሌን ቀድም በማለት የግላቸው ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ አራተኛ ፈራሚያቸው አድርገው አጥቂው መሳይ ሠለሞን ተቀላቅለዋል።

ከዚህ ቀደም በሰንዳፋ በኬ ፣ ቡታጂራ ከተማ እና ገላን ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ በቡድኑ ቆይታው ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማድረግ የቻለ ሲሆን በቀጣይ ደግም በፕሪምየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጫወት ወላይታ ድቻን ተቀላቅሏል።