ዐፄዎቹ የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ፋሲል ከነማ ለከርሞ እራሱን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በመግባት የመጀመርያ ፈራሚውን አግኝቷል።


በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ስድስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት የመጀመርያ ፈራሚያቸውን ባለፈው የውድድር ዓመት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ቆይታ የነበረው አማካዩ በረከት ግዛውን አስፈርመዋል።

በሀያ ሦስት ጨዋታዎች ለ1339 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አማካዩ ጂንካ ከተማን ከለቀቀ በኋላ ባመራባቸው ኢትዮጵያ መድን ድርጅትና ንግድ ባንክን በተከታታይ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድጉ ጉልህ አስተዋጾ ማበርከቱ ሲታወስ ዘንድሮም በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መልካም ጊዜ በማሳለፍ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ችሏል። አሁን ደግሞ ከባንክ ጋር የነበረውን የሁለት ዓመታት ቆይታ አገባዶ የህክምና ምርመራውን በማድረግ የፋሲል ከነማ የመጀመርያው ፈራሚ ሆኗል።