አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ በነብሮቹ ቤት የሚያቆያቸውን ውል አድሰዋል።
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን 8ኛ ደረጃ ላይ በ41 ነጥቦች ያጠናቀቀው ሀድያ ሆሳዕና በቀጣዩ የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ በደቡብ አፍሪካ ከነበረው የገቢ ማሰባሰብ እና የወዳጅነት ጨዋታ መልስ የአሰልጣኝ ግርማ ታደሠን ውል በማደስ ቀዳሚ ስራውን ጀምሯል።
ሀድያ ሆሳዕናን በሁለት አጋጣሚዎችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉት አሰልጣኙ ከደቡብ ፓሊስ ፣ ሀምበሪቾ እና ስልጤ ወራቤ ከነበራቸው ቆይታ በኋላ በ2015 የውድድር ዓመት በረዳት አሰልጣኝነት ወደ ሀድያ ሆሳዕና በመመለስ ማገልጠል የጀመረ ሲሆን በተጠናቀቀው ዓመት ደግሞ የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን መልቀቅ ተከትሎ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል። በቀጣዩ የውድድር ዘመንም ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ ለአንድ ዓመት ውላቸው በክለቡ ታድሶላቸዋል።