ፋሲል ከነማ አማካይ ለማስፈረም ተስማማ

በስምምነት ደረጃ የተለያዩ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ፋሲል ከነማ አንድ አማካይ ለማስፈረም ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት ፋሲል ከነማዎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በዝውውር ገበያው ላይ እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለፉትን ሁለት ዓመታት ጥሩ የውድደር ዓመት ያሳለፈው አሚር ሙደሲር ዐፄዎችን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

በኢትዮጵያ መድን ታዳጊ ቡድን መነሻውን ያደረገው አሚር በኢኮስኮ እና ገላን ቆይታ ካደረገ በኋላ ነበር ዳግም ወደ አሳዳጊው ክለብ ኢትዮጵያ መድን በመቀላቀል ቡድኑ ወደ ሊጉ እንዲያድግ ካስቻሉ ቁልፍ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን የቻለው። አሚር ሁለት ዓመት ከቆየበት ኢትዮጵያ መድን ጋር በመለያየት ለቀጣዩ ሁለት ዓመት በዐፄዎቹ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።