ድሬደዋ ከተማ የዋና አሰልጣኙ ቅጥር አስመልክቶ የተሰጠው ዝርዝር የጋዜጣዊ መግለጫ

ዛሬ ጠዋት በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የሁለቱ አካላት የስምምነት የፊርማ ሥነ ስርዓት ላይ የከለቡ ፕሬዝደንት ኢንጅነር ከማል ኢብራሂም ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ እስከዳር ዳምጠው፣ እና የክለቡ የቦርድ አባል እና የቀድሞ ተጫዋች ፉአድ ኢብራሂም ክለቡን በመወከል እንዲሁም አዲስ ለቡድኑ የተሾሙት አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በመድረኩ ላይ ሲሰየሙ ጥሪ የተደረገላቸው የሚዲያ አካላት በስፍራው ተገኝተዋል።

ድሬደዋ ከተማዎች አሰልጣኝ ይታገሱን የመረጡበት ምክንያት

– በወጣቶች የተገነባ የድሬደዋ እሴትን የሚያስጠብቅ የጨዋታ ፍልስፍና መንገድ የሚከተል በመሆኑ

– የድሬደዋ ወጣቶችን ወደ ትልቅ የእግርኳስ ደረጃ(እስከ ብሔራዊ ቡድን) ያሸጋግራል የሚል ስምምነት በመድረሳቸው

– ለተለያዮ ያልተገባ የጎንዮሽ ስራዎች የማይወድ ከሙስና የፀዳ በመሆኑ

– ጠንካራ የዲሲፒሊን መርህ ተከታይ በዲሲፒሊን የማይደራደር ክለቡ ከሚፈልገው መርህ ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ እንዲሁም በሜዳ ላይ ለቴክኒካሊ ዲሲፒሊን ያላቸው አቋም

– ተጫዋቾችን የማሳደግ፣ የማሻሻል አቅም እንዳለው በማመን እና በመረዳት

– ለቀድሞ ክለቡ(ለአዳማ ከተማ) ያለው ታማኝነቱ ፕሮፌሽናል አስተሳሰቡ የክለቡን ኮንትራት ሳይጨርስ ለመደራደር ፍቃደኛ አለመሆኑ ድሬደዋን የገዛው እና ዋናው የሳበው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ድሬደዋ ከተማ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ለረዥም ጊዜ ለአራት ዓመታት ያስፈረመበት ምክንያት

– በወጣቶች ላይ ባለው እምነት እና በቀጣይ ሁለት ሦስት ዓመታት ላይ ድሬደዋ ትልልቅ ለብሔራዊ ቡድን ድረስ መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾችን ማውጣት እንዲቻል

– ለአሰልጣኞች የሚሰጠውን አጭር ጊዜ በመቀየር ሰፊ ጊዜ በመስጠት ተከታታይነት ያለው ጠንካራ ቡድን ለመስራት

አጠቃላይ የድሬደዋ እግርኳስን የመለወጥ በቂ ጊዜ ለመስጠት

– ወጥነት ያለው የተረጋጋ ቡድን ለመገንባት

አሰልጣኝ ይታገሱ የብዙ ቡድኖች ፍላጎት ቢኖርም የድሬደዋን ጥያቄ በመቀበል ለማሰልጠን የተስማማበት ምክንያት

– ከከፍተኛ አመራሩ ከከንቲባው ጀምሮ ህዝቡ ለእግርኳስ ያላቸው ፍቅር እና ዕገዛን በማሰብ

– ድሬደዋ ብዙ ተስዕጦ ያላቸው ወጣቶችን ማግኘት የሚቻልበት አካባቢ በመሆኑ

– የድሬደዋ ከተማን የቀድሞ ዝናዋን ስሟን ለመመለስ በማሰብ

– ካሳደገው አዳማ ከተማ በመውጣ ለሌላ ፈተና እራሳቸውን ለማሳየት በማሰብ ቡርትካናማዎቹን መምረጣቸውን አንስተዋል።

አሰልጣኝ ይታገሱ ለአራት ዓመታት ቡድኑን በሚያሰለጥኑበት ወቅት ዕቅዳቸው ምድን ነው ?

ወጥነት፣ ተከታታይነት ያለው ቡድን ለመስራት እና ድሬደዋ የምትታወቅበት የራሷን ቃና(ስልት) ኳስን ተቆጣጥሮ መጫወት ዋናው የስምምነቱ አካል መሆኑን እና ያም ቢሆን ውጤት ያስፈልጋል ስለዚህም ሊጉ ላይ መቆየት እንዳለ ሆኖ በየ ዓመቱ ከፍ እያለ ከሁለት ከሦስት ዓመት በኋላ ለዋንጫ የሚጫወት ቡድን መገንባት። ታዳጊዎች ከ17ዓመት በታች ጀምሮ መስራት በተጨማሪም በድሬደዋ በሚደረጉ የዲቪዚዮን ውድድሮች አቅም ያላቸውን ተጫዋቾችን ማብቃት። የድሬደዋ ህዝብ ደጋፊው ክለቡን ጨምሮ ከመውጣት እና መውረድ ጋር ተያይዞ ካለው የስነ ልቦና ስሜት ማጥፋት ዕቅዳቸው እንደሆነ አሰልጣኙ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ድሬደዋ ከተማ ለአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በወር 305.000 ሺህ ያልተጣራ ደሞዝ እንደሚከፍል በመናገር የፊርማ እና 2020 የሚል ማልያ በመያዝ የፎቶ ሥነ ስርዓት ተካሂዶ የመርሐ ግብሩ ፍፃሜ ሆኗል።