በካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ተካፋዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሁለት ነባሮችን ውልም አድሷል።
የ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር የዋንጫ አሸናፊው ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያን በመወከል በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ጨዋታ ላይ ይሳተፋል። በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የሚመራው ክለቡ በትላንትናው ዕለት ቅድስት ዘለቀን ፣ ታሪኳ ዴቢሶ ፣ ሳራ ነብሶ ፣ ንግስት በቀለ እና መሠረት ወርቅነህን ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የሁለቱን ነባሮች ውልም አራዝሟል።
አማካዩዋ ሲሳይ ገብረዋህድ ማረፊያዋ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል። ከኢትዮ ከኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ከተገኘች በኋላ በመቻል ፣ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ደግሞ የተጠናቀቀውን ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ አሳልፋለች።
ሌላኛዋ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሂሩት ሒሩት ተስፋዬም የንግድ ባንከሸ ሌላኛዋ ፈራሚ ነች። ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ የተገኘችው እና ቦሌ ክፍተ ከተማ እና የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ተጫውታ በማሳለፍ ቀጣዩ ክለቧ ንግድ ባንክ ሆኗል።
ቡድኑ ከሁለቱ አዳዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ የተከላካዩዋ ናርዶስ ጌትነት እና የመስመር አጥቂዋን መሳይ ተመስገንን ውል ለተጨማሪ ዓመት ቡድኑ አራዝሟል።