አርባምንጭ ከተማ የሦስት ተጫዋቾቹን ውል አድሷል

በአሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመሩት አዞዎቹ የሦስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል አራዝመዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም የተመለሰው አርባምንጭ ከተማ ከቀናቶች በፊት ሳሙኤል አስፈሪ ፣ አካሉ አትሞ ፣ በፍቅር ግዛቸው እና በትላንትናው ዕለት ደግሞ የአጥቂው አህመድ ሁሴንን ውል ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሦስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ኮንትራት አድሰዋል።

ወደ ቀድሞው ክለቡ በ2014 አጋማሽ ላይ የተቀላቀለው የቀድሞው የሲዳማ ቡና ፣ መቻል እና ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ አበበ ጥላሁን ፣ ከጋሞ ጨንቻ የተገኘው እና በአርባምንጭ ላለፉት አራት ዓመታት ቆይታ የነበረው ሌላኛው ተከላካይ አሸናፊ ፊዳ እና ወጣቱ አማካይ ቡታቃ ሸመና በቡድኑ ውስጥ ውላቸው ታድሶላቸዋል።