የመስፍን ታፈሰ ጉዳይ

ደቡብ አፍሪካ ለሙከራ ተጉዞ የነበረው የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰ…

ከሳምንት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሺፕ ከሚገኘው ፖሎኩዋኔ ሲቲ የሙከራ ዕድል ተመቻችቶለት ወደ ስፍራው ያቀናው የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሠ ዛሬ ከሰዓት ወደ ሀገር ቤት መመለሱ ታውቋል። መስፍን በደቡብ አፍሪካ ስለነበረው የሙከራ ቆይታ በምን መልኩ እንደነበረ ለማወቅ ወኪሉን አዛርያስ ተስፋፂዮን አናግረነው እንደነገረን ከሆነ በመስፍን ዙውውር ዙርያ ክለቡ በአንዳንድ ጥቅማጥቅሞች ዙርያ ከስምምነት መድረስ ባለመቻሉ ዝውውሩ አልተሳካም።

በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኘው መስፍን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የውል ዘመኑ መጠናቀቁ ተከትሎ በቡናማዎቹ ቤት ይቆያል ወይስ ወደ ሌላ ክለብ ያመራል የሚለው ጉዳይ ትኩረትን የሚስብ ይሆናል።