የጣና ሞገዶቹ የአማካያቸውን ውል አድሰዋል

ባህር ዳር ከተማዎች የተከላካይ አማካያቸውን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘማቸው ታውቋል።

በአሠልጣኝ ደግአረገ የሚመሩት ባህር ዳር ከተማዎች እስካሁን በይፋ የዝውውር መስኮቱን ባይቀላቀሉም ቡድናቸውን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከቀናት በፊት የፍፁም ፍታለው እና ይኸነው የማታን ውል ማደሳቸው አይዘነጋም። አሁን ደግሞ ክለቡ የተጨማሪ አማካዩን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘሙ ታውቋል።

ውሉን ያራዘመው ተጫዋች በረከት ጥጋቡ ነው። የቀድሞ የአማራ ፖሊስ፣ ኢኮስኮ እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች የነበረው በረከት ከአራት ዓመታት በፊት ወደ ባህር ዳር ከተማ አምርቶ የነበረ ሲሆን በተለይ ዘንድሮ በሁለተኛው ዙር በቋሚነት ክለቡን ሲያገለግል ተስተውሏል። ተጫዋቹም ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ ጋር ሲያደርግ የነበረውን ድርድር አጠናቆ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል።