ግርማ ዲሳሳ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመቻል ቤት ያሳለፈው የመስመር ተጫዋች ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ስምምነት ላይ ደርሷል።

ዘግየት ብለው ወደ ዝውውር መስኮቱ በመግባት በዛሬው ዕለት ወንድሜነህ ደረጄን የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ያደረጉት ባህር ዳር ከተማዎች ሁለተኛ ፈራሚ ለማግኘት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል።

ቡድኑን ዳግም ለመቀላቀል የተስማማው ሁለተኛው ተጫዋች የመስመር ተጫዋቹ ግርማ ዲሳሳ ነው። የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ተጫዋች ያለፉትን ሁለት ዓመታት ካገለገለበት መቻል በፊት ዘለግ ያሉ ዓመታትን በትውልድ ከተማው ባህር ዳር ከተማ የተጫወተ ሲሆን አሁን ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ስምምነት ላይ ደርሷል።