ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል

በዝውውር ገበያው በቀዳሚነት የተሳተፉት ሲዳማ ቡናዎች ሦስተኛ ፈራሚያቸው እንዲሆን ከግራ መስመር ተከላካዩ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ከሊጉ ክለቦች ወደ ዝውውር ገበያው ቀድሞ በመግባት አበባየሁ ሀጂሶ እና ሳሙኤል ሳሊሶን በተጨማሪም የተከላካዩ ደስታ ደሙን ውል በማራዘም የተንቀሳቀሰው ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርቧል።

ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል የተስማማው ፍራኦል መንግስቱ ሲሆን ተጫዋቹም የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቅ በአብዛኛዎቹ ድርድሮች በመስማማት የሲዳማ ቡናን የመከላከል አደረጃጀት ለማጠናከር ፊርማውን ማኖር ብቻ ይቀረዋል።

በሀድያ ሆሳዕና ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሀላባ እና አዲስ አበባ የተጫወተው ተጫዋቹ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ግልጋሎት ከሰጠ በኋላ ከሲዳማ ቡና ጋር ለሁለት ዓመታት ቆይታ ለማድረግ መስማማቱ ታውቋል።

ሲዳማዎች በቀጣይ ጊዜያት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እንደሚቀላቅሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።