ሲዳማ ቡናዎች የወሳኙ አጥቂያቸውን ውል አራዘሙ

ሲዳማ ቡና የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነውን አጥቂን ውል ማራዘሙ ታውቋል።

በዝውውሩ እጅግ የጎላ እንቅስቃሴ በማድረግ በርከት ያሉ ዝውውሮች እየፈፀሙ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ የጋናዊውን የመስመር አጥቂ ማይክል ኪፕሩቪን ውል ለተጨማሪ ዓመታት አራዝመዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ክለቡን ተቀላቅሎ ቡድኑ በሊጉ እንዲተርፍ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረገው ይህ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዓመት በሀያ ስድስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሰባት ግቦች በማስቆጠር የክለቡ ከፍተኛ ጎል አግቢ በመሆን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ለሀገሩ ክለቦች ሶንዲሱ እና ኢንተር አላይንስ ፣ በሴኔጋሉ ኤ ኤስ ሲ ጄርፍ ፣ በሱዳኑ ኤልሜሪክ ፣ በአይቮሪኮስቱ አፍሪካን ስፖርትስ ግልጋሎት መስጠት የቻለ ሲሆን ወደ ህንድ በማምራትም አራት ዓመታትን በቢ ኤስ ኤስ እና በኔሮካ ተጫውቶ በማሳለፍ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ሲዳማን በመቀላቀል በግሉ ጥሩ ቆይታን ማድረጉ ይታወሳል።