መስፍን ታፈሠ ሲዳማ ቡናን ተቀላቀለ

በዝውውሩ የነቃ ተሳታፊ የሆነው ሲዳማ ቡና ፈጣኑን አጥቂ የግላቸው አድርገዋል።

በዝውውር ገበያው የነቃ ተሳትፎን በማድረግ ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከአበባየሁ ሀጂሶ ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ ፣ ፍራኦል መንግስቱ እና ያሬድ ባዬ በመቀጠል ሌላኛው አዲሱ ፈራሚያቸው ፈጣኑ አጥቂ መስፍን ታፈሠ ሆኗል።

ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ፓሎኩዋኔ የሙከራ ጊዜን አድርጎ የተመለሰው የመስመር እና የፊት አጥቂው መስፍን ታፈሠ ከሀዋሳ የዕድሜ ዕርከን ቡድኖች የተነሳው የእግር ኳስ ህይወቱ በ2011 መጋቢት ወር ላይ የክለቡ ዋናውን ቡድን በመቀላቀል ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጋር መተዋወቅ የቻለ ሲሆን በአሳዳጊ ክለቡም ከታዳጊ ቡድን አንስቶ የስድስት ዓመታት ቆይታን ካደረገ በኋላ 2015 ወደ ኢትዮጵያ ቡና በማምራት በክለቡ ግልጋሎት እየሰጠ የነበረ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ መዳረሻው ሲዳማ ቡና ሆኗል።