ኢትዮጵያ ቡና የተከላካዩን ውል አራዝሟል

በርካታ ተጫዋቾችን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ የሰጠው ኢትዮጵያ ቡና የተከላካዩን ውል አራዝሟል።

በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ መሪነት ጥቂት በቡድኑ የቀሩ ወጣት ተጫዋቾችን እና ከከፍተኛ ሊጉ የፈረሙ ተጫዋቾችን በመያዝ ለአህጉራዊ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በክለቡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታ የነበረውን የመሐል ተከላካይ ወልደአማኑኤል ጌቱን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል።

ከሐረር ሲቲ በኋላ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሰበታ ከተማ በመጫወት ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ ሲጫወት የነበረው ተከላካዩ ለቀጣዩ ሁለት ዓመታትም በቡድኑ ውስጥ እንደሚቆይ ዕርግጥ ሆኗል።

ቡድኑ ከአንድ ቀን በፊት ደግሞ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ የሆነውን ፀጋዘአብ አስገዶምን ውል ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ማራዘማቸውን ይታወሳል።