ሲዳማ ቡና አማካይ አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ታውቋል።


በ2017 የውድድር ዘመን ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሲዳማ ቡናዎች አበባየሁ ሀጂሶ ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ ፣ ፍራኦል መንግሥቱ እና ያሬድ ባዬህን አስፈርመው የደስታ ደሙን ውል ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የተከላካይ አማካይ ወደ ስብስባቸው እንደቀላቀሉ ታውቋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ሬድዋን ናስር ነው። በአዲስ አበባ ከተማ በታዳጊ እና በዋናው ቡድን ውስጥ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ታላቅ ወንድሙ አቡበከር ናስር በነገሠበት ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ያለፉትን አምስት ዓመታት ከተጫወተ በኋላ ማረፊያውን ሲዳማ ቡና ለሁለት ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።