አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቀጣይ መዳረሻው ይፋ ሆኗል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን ያለፈውን ዓመት የውድድር ዘመን በሁለት መልክ ያጠናቀቁ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመት ግን ተጠናክሮ ለመቅረብ ክለቡን እየለቀቁ ባሉ ተጫዋቾች ምትክ ሊሆኑ የሚችሉ ተጫዋቾችን ለማግኘት ወደ ዝውውሩ በመግባት ቀዳሚ ፈራሚያቸው አማካዩ ዳዊት ተፈራ ሆኗል።
ከሻሸመኔ የተነሳው የእግር ኳስ ህይወቱን በማስከተል መቻል ፣ በሲዳማ ቡና እና ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ከክለቡ ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለው አማካዩ አዲሱ የመድን ተጫዋች መሆኑን በሁለት ዓመት ውል አረጋግጧል።
ቡድኑ ከዳዊት ተፈራ በፊት የወሳኝ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ እና የወጣቱን አጥቂ መስፍን ዋሼን ኮንትራት ማደሱ ይታወሳል።