ወላይታ ድቻ የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል

በከፍተኛ ሊጉ የቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታ ላይ ሲጫወት የነበረው ተጫዋች ወላይታ ድቻን በዛሬው ዕለት ተቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹው መሪነት ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ሙሉቀን አዲሱ ፣ ቴዎድሮስ ታፈሠ ፣ መሳይ ሠለሞን እና ውብሸትን ክፍሌን ያስፈረሙት እና የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሱት ወላይታ ድቻዎች በዛሬው ዕለት ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካይ የሆነውን ምንተስኖት ተስፋዬን አምስተኛ ፈራሚ አድርገውታል።

በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ነገሌ አርሲ የተጠናቀቀውን ዓመት ያሳለፈው ተጫዋች ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዘመናት ደግሞ ማረፊያው ወላይታ ድቻ ሆኗል።