ነሐሴ 11 የሚደረገውን የቪላ እና የባንክ የቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ተለይተዋል።
አህጉራዊ የክለብ ውድድሮች ከእረፍት መልስ ዳግም ሊመለሱ ሲሆን ታላቁ የአህጉራችን የክለቦች ውድድር የሆነው ቻምፒየንስ ሊግም በቀጣዩ ወር የቅድመ ማጣሪያ ፍልሚያዎችን ማከናወን ይጀምራል። ኢትዮጵያን የሚወክለው የኢትዮጵያው ሻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ በዚህ የቅድመ ማጣሪያ የሚሳተፍ ሲሆን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከውነውን ጨዋታም ከዩጋንዳው ሻምፒዮናው ስፖርትስ ክለብ ቪላ ጋር ያደርጋል።
የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታ ነሐሴ 11 ካምፓላ በሚገኘው ማንዴላ ብሔራዊ ስታዲየም (የተፈጥሮ ሳር) ሲደረግ ጨዋታውንም አራት ዛምቢያዊ አልቢትሮች እንዲመሩት መመደቡ ታውቋል።
ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ሂላሪ ሀምባባ፣ በረዳትነት ደግሞ ሜክ ዙሉ እና ቶማስ ካኤላ እንዲሁም በአራተኛ ዳኝነት ቾላ ቻንዳ ግልጋሎት እንዲሰጡ ከጁቡቲያዊው ኮሚሽነር ሞሐመድ ሞሚን ዓሊ ጋር ተደልድለዋል።