ሀድያ ሆሳዕና የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚውን አግኝቷል

ነብሮቹ የመስመር አጥቂውን ቀዳሚ አዲሱ ተጫዋቻቸው አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳዳሪው ክለብ ሀድያ ሆሳዕና ከደቡብ አፍሪካው የወዳጅነት እና የገቢ ማሰባሰብ መርሀግብር መልስ የአሰልጣኝ ግርማ ታደሠን ውል በማራዘም በማስከተል ደግሞ በትላንትናው ዕለትም የቃለአብ ውብሸት ፣ ከድር ኩሊቫሊን እና ሳሙኤል ዮሐንስ ውል ያደሱ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ የተጫዋቾች ግዢ በመግባት የመጀመሪያ ፈራሚያቸው የመስመር አጥቂው እዮብ አለማየሁ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን መነሻውን ያደረገው እና 2008 በዋናው ቡድንም ጭምር ግልጋሎት የሰጠው ተጫዋቹ ከገጠመው ጉዳት ካገገመ በኋላ በጅማ አባጅፋር እንዲሁም ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በሀዋሳ ከተማ መለያ ቆይታን አድርጎ ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዘመናት መዳረሻው ሀድያ ሆሳዕና ሆኗል።