ጫላ ተሺታ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

ሀድያ ሆሳዕና ሦስተኛ ፈራሚውን አግኝቷል።

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ ውል ማራዘም በኋላ የቃለአብ ውብሸት ፣ ከድር ኩሊባሊ ፣ መለሠ ሚሻሞ እና ሳሙኤል ዮሐንሰን ውል በማራዘም እንዲሁም ደግሞ እዮብ ዓለማየሁ እና በረከት ወንድሙን በእጃቸው ያስገቡት ሀድያ ሆሳዕናዎች የመስመር አጥቂው ጫላ ተሺታን ሦስተኛው ፈራሚ በማድረግ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

በሻሸመኔ ከተማ እግር ኳስን የጀመረው እና በሰበታ ከተማ ግልጋሎት የሰጠው ጫላ ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ከተጫወተ በኃላ 2010 ላይ ወደ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሎ መጫወት የቻለ ሲሆን በውሰት ለአዳማ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል። በሲዳማ ቡና በሁለት አጋጣሚዎችን ግልጋሎት የሰጠው ተጫዋቹ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በኢትዮጵያ ቡና ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ነብሮቹ ቤት ሆኗል።