ባህር ዳር ከተማ ሦስተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት ባህርዳር ከተማዎች የክረምቱ ሦስተኛው ፈራሚ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣይ ዓመት ተሳትፎውን ባጣቸው በርካታ ተጫዋቾች ምትክ የሚሆኑ አዳዲስ ፈራሚዎችን ወደ ቡድኑ እያካተተ የሚገኘው የጣናው ሞገድ ከግርማ ዲሳሳ እና ወንድሜነህ ደረጀ በመቀጠል የክረምቱ ሦስተኛ ፈራሚያቸው አጥቂው አቤል ማሙሽ ሆኗል።

232 ደቂቃዎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መለያ በፕሪምየር ሊጉ ያገለገለው አጥቂው ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ በከፍተኛ ሊጉ በቡድኑ ውስጥ አበርክቶው ከፍ ያለ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከወራቶች በፊት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ከንግድ ባንክ ጋር ከተለያየ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ግን ባህርዳር ከተማ ሆኗል።