ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን ተጫዋች በእጁ አስገብቷል

ወጣቱ የመስመር አጥቂ ማረፊያው የሐይቆቹ ቤት ሆኗል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣዩ ዓመት ተሳትፎአቸውን አጠናክረው ለመቅረብ ወደ ዝውውሩ በመግባት ቢኒያም በላይ ፣ ወንድማገኝ ማዕረግ እና ወንድማገኝ ሐይሉን በይፋ ያስፈረሙት ሀዋሳ ከተማዎች በዛሬው ዕለት ደግሞ ወጣቱን የመሰመር አጥቂ ዮሴፍ ታረቀኝ ማስፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ክለቡ ከላከላት መረጃ መመልከት ችላለች።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ከሆኑ ወጣት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ከመቂ የተገኘው ዮሴፍ ታረቀኝ በአዳማ ከተማ ላለፉት ሦስት ዓመታት መድመቅ የቻለ ሲሆን በክለቡ ቆይታውም በ2015 የውድድር ዘመን የዓመቱ ምርጥ ተስፈኛ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል። ከእናት ክለቡ አዳማ ጋር ቀሪ አንድ ዓመት ቢኖረውም በደመወዝ አለመከፈል ምክንያት መልቀቂያውን ከፌድሬሽኑ ያገኘው ተጫዋቹ ቀጣዩ ክለቡ ሀዋሳ መሆኑ ዛሬ ተረጋግጧል።