ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት የመስመር አጥቂዎችን አስፈርሟል

የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታው ኢትዮ ኤሌትሪክ ሁለት የመስመር አጥቂዎችን የቡድኑ አካል አድርጓል።

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም የተመለሱት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ቡድናቸውን ለማጠናከር ከነባር ተጫዋቾች ውል ማደስ በተጨማሪ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን ትናንት አመሻሹን ደግሞ ሁለት የመስመር አጥቂዎችን አሸናፊ ጥሩነህ እና እዮብ ገብረማርያምን በይፋ ወደ ስብሰቡ ቀላቅሏል።

የቀድሞው የኮምቦልቻ እና ገላን ከተማ ተጫዋች ኢትዮጵያ መድንን በ2014 ከተቀላቀለ በኋላ እስከ 2015 የውድድር ዘመን ድረስ በፕሪምየር ሊጉ ከመድን ጋር ቆይታ የነበረው ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ከሻሸመኔ ከተማ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታን ካደረገ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው ኤሌክትሪክ ሆኗል።

አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን በሲዳማ ተስፋ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ከዘለቀ በኋላ ወደ በሻሸመኔ በማምራት ያለፉትን አምስት ቆይታ በማድረግ አሸናፊ ሻሸመኔ ወደ ሊጉ ሲያድግ ትልቅ ድርሻ የነበረው ሲሆን ዘንድሮም በፕሪሚየር ሊግ ቡድኑን ሲያገለግል ቆይቶ ለከርሞ ማረፊያው ኤሌክትሪክ መሆኑ ተረጋግጧል።