አዳማ ከተማ አዲሱን አሰልጣኝ አሳውቋል

የአዳማ ከተማ ቀጣዩ ዋና አሰልጣኝ ታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው አዳማ ከተማ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ መሪነት በ44 ነጥቦች ሊጉን 7ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቀቻው ይታወሳል። ሆኖም ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ዋና አሰልጣኙ ወደ ድሬዳዋ በማምራቱ በቦታው ለመተካት ሁለት አሰልጣኞችን ለመሾም ሲመለከት ቆይቶ ትናንት አመሻሹን አሰልጣኝ አብዲ ቡሊን በኃላፊነት ቡድኑ ስለ መሾሙ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ የደረሳት መረጃ አመላክቷል።

እግርኳስን በተጫዋችነት ዘመናቸው በሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ የዝዋዩ ኢትኮ እና አዳማ ከተማ ውስጥ በአማካይ ቦታ ላይ በመጫወት ያሳለፉት አሰልጣኙ ወደ ስልጠናው አለም ከገቡ በኋላ የዝዋዩ ኢትኮን ፣ ባቱ ከተማን ፣ ቡራዩ ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት የመሩ ሲሆን ባለፉትት አራት ዓመታት ደግሞ የአዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ እንዲሁም ደግሞ በቡድን መሪነት ክለቡን ሲያገለግሉ ቆይተው አመሻሹን ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ክለቡ ሾሟቸዋል።