በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል።
የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ሁለት ተቃራኒ የውድድር መልኮችን በመያዝ በመጨረሻም በሁለተኛው ዙር ውጤቶች ታግዞ በሰበሰባቸው 40 ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የቋጩት የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌው ኢትዮጵያ መድን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ የቅድመ ውድድር ዝግጅታውን መቼ እንደሚጀምሩ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዝውውር መስኮቱ ዳዊት ተፈራ ፣ ዮሐንስ ሱጌቦ እና ያሬድ መሐመድን እስከ አሁን የስብስቡ አካል ያደረገው እና የአቡበከር ኑራ ፣ መስፍን ዋሼ ፣ ዋንጫ ቱት እና የዳዊት አውላቸውን ውል ለተጨማሪ ዓመት ያራዘመው ክለቡ ከዛሬ ጀምሮ የቡድኑ አባላት መቀመጫቸውን በአዳሜ ራስ ሆቴል በማድረግ ከነገ ዕሮብ ነሐሴ 01 ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ።