የጦና ንቦቹ ዝግጅታቸውን ሊጀምሩ ነው

ወላይታ ድቻ ከአንድ ቀን በኋላ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ይጀምራል።

ያለፈውን ዓመት ደከም ባሉ የውድድር ጉዞ ውስጥ ሆኖ ዓመቱን በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ በሰበሰባቸው 34 ነጥቦች ተቀምጦ ያጠናቀቀው ወላይታ ድቻ ለ2017 የውድድር ዘመን የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሊጀምሩ ስለ መሆኑ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት የጦና ንቦቹ ሙሉቀን አዲሱ ፣ ቴዎድሮስ ታፈሠ ፣ ውብሸት ክፍሌ ፣ መሳይ ሠለሞን እና ምንተስኖት ተስፋዬን ያሬድ ዳርዛ የስብሰባቸው አካል ያደረጉ ሲሆን ከቀናት በኋላ ከሚፈፅሙት የተከላካይ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዝውውር በፊት ግን የቅድመ ውድድር ዝግጅትን ይጀምራሉ።

የቡድኑ አጠቃላይ አባላት በነገው ዕለት ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክለቡ ካምፕ ከተሰባሰቡ በኋላ ሐሙስ ነሐሴ 2/2016 ክለቡ ውድድር ዘመኑ ዝግጅቱን መከወን ይጀምራል።