ፍፁም ዓለሙ ወደ ቀድሞው ክለቡ ለመመለስ ተስማማ

ባህር ዳር ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን አራተኛው አዲሱ ተጫዋች አድርጓል።

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው መሪነት ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሳቸውን ለማጠናከር በክረምቱ የዝውውር መስኮት ግርማ ዲሳሳ ፣ ወንድሜነህ ደረጀን እና አቤል ማሙሽን የግላቸው ያደረጉት ባህር ዳር ከተማዎች የቀድሞው የአማካይ እና የመስመር አጥቂ ስፍራ ተጫዋቹን በእጃቸው ለማስገባት ስምምነት ፈፅመዋል።

ወደ ክለቡ ማምራት ከጫፍ የደረሰው ተጫዋች ፍፁም ዓለሙ ነው። በክለብ ደረጃ ለጥቁር አባይ ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፣ ባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ ፈጣን ተጫዋች ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናትን ከቆየበት መቻል ወደ ቀደመ ክለቡ ባህርዳር ከተማ መመለሱ ዕውን ሆኗል።