ፈረሰኞቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

በከፍተኛ ሊጉ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው የመስመር አጥቂ ማረፊያው ፈረሰኞቹ ቤት ሆኗል።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች ለከርሞ ቡድናቸውን ለማጠናከር የዋና አሰልጣኝ ለመሾም ትኩረት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት ጎን ለጎን አዳዲስ ተጫዋችን ማምጣታቸውን ቀጥለው የመጀመርያ ፈራሚያቸው ፍፁም ጥላሁን ማድረጋቸው ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ ሁለተኛ ፈራሚያቸውን የመስመር አጥቂውን ፀጋ ከድርን ሆኗል። በሦስት ዓመት ውስጥ ከሀላባ ተስፋ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ፀጋ በዘንድሮ ዓመት ከመስመር እየተነሳ ስድስት ጎሎች ያስቆጠረ ሲሆን ወደ ፊት ተስፋ የሚጣልበት ወጣት ተጫዋች መሆኑን በከፍተኛ ሊጉ አሳይቷል። ፀጋ ለሁለት ዓመታት በቡድኑ የሚያቆየውን ስምምነት መፈፀሙን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ፈረሰኞቹ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ለማምጣት ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ።