የጣናው ሞገዶቹ ነገ በአዳማ ዝግጅታቸውን መከናወን ይጀምራሉ

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት ባህርዳር ከተማዎች ሐሙስ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በይፋ ይጀምራሉ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያለፈውን ዓመት ቆይታ በ50 ነጥቦች አራተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ባህርዳር ከተማዎች ለ2017 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው መሪነት ራሳቸውን ለማጠናከር በክረምቱ የዝውውር መስኮት ግርማ ዲሳሳ ፣ ወንድሜነህ ደረጀ ፣ አቤል ማሙሽ እና ፍፁም ዓለሙን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን የበረከት ጥጋቡ ፣ ይሄነው የማታ እና ፍፁም ፍትህአለሙን ኮንትራት ደግሞ ማደሳቸው ይታወቃል።

በቀጣዩቹ ቀናት ምናልባት አንድ አዲስ ተጫዋቾች እንደሚያስፈርም የሚጠበቀው ቡድኑ በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ይጀምራል። በዛሬው ዕለት የቡድኑ አባላት መቀመጫቸውን በአዳማው የባ ሆቴል በማድረግ በማግስቱ ሐሙስ ነሐሴ 2/2016 በይፋ ዝግጅታቸውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ሜዳ ላይ ይጀምራሉ።