አርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

የአሰልጣኝ በረከት ደሙው አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ አራተኛ ፈራሚውን አግኝቷል።

በፕሪምየር ሊጉ ከአንድ ዓመት በኋላ የተመለሰው አርባምንጭ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሳቸውን ለማጠናከር ይረዳቸው ዘንድ ይሁን እንዳሻው ፣ ሙሉጌታ ካሳሁን እና ካሌብ በየነን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ግብ ጠባቂው ፋሪስ ዕላዊን አራተኛ ፈራሚ አድርገዋል።

በቤንች ማጂ ቡና በነበረው አመርቂ እንቅስቃሴ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያለፉትን ሦስት የውድድር ዘመናት በወልቂጤ ከተማ ያሳለፈው ይህ ቁመታሙ የግብ ዘብ ቀጣይ መዳረሻውን አዞዎቹ ቤት አድርጓል።

በቀጣዮቹ ቀናት ሦስት የውጪ ሀገር ዜጋን ጨምሮ አንድ የሀገር ውስጥ አጥቂን ክለቡ እንደሚያስፈርም ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቋል።