የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ተራዘመ

የፊታችን እሁድ እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ጨዋታ ተራዘመ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸፊናው ኢትዮጵያ ቡና የሚያካሂዱት ተጠባቂው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ላይተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ፌደሬሽኑ በይፋዊ ገፁ አስታውቋል።

በቀጣይ እሁድ እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ይህ ጨዋታ የተራዘመበት ምክንያት እና የሚካሄድበት ዕለት አልተገለፀም። ፌደሬሽኑ በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታው እንዲራዘም በደብዳቤ ገልፆ እንደነበር በመጥቀስ ቡድኖች በቂ መዘጋጃ እንዲያገኙ ከጨዋታው አንድ ወር አስቀድሞ በመገለፁ እንዲሁም ጨዋታውን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ በመግለፅ ጨዋታው በተያዘለት ዕለት እንደሚካሄድ ቢገልፅም አሁን ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ አስታውቋል።