የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ መድኖች የቀኝ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል።
የአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌን ኮንትራት ከወራት በፊት አስቀድመው ማራዘም የቻሉት መድኖች ለ2017 የውድድር ዘመን ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርመው የአምስት ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ከትናት በስቲያ በአዳማ ዝግጅታ መጀመራቸው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ አራተኛ ተጫዋች በመሆን የመስመር ተከላካዩን ዳግማዊ አባይን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ በወልድያ እና በሀምበሪቾ ያሳለፈው እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድግ የበኩሉን ድርሻ የተወጣው ተጫዋቹ ዘንድሮ ከድሬደዋ ከተማ ጋር አመዛኙን ጨዋታ በመጫወት ግልጓሎት የሰጠ ሲሆን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም በስምምነት በመለያት ወደ ኢትዮጵያ መድን የሚያደረገውን ዝውውር ለማጠናቀቀ የህክምና ምርመራ አድርጎ ፊርማውን ለማኖር መቃረቡን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።