ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

አሰልጣኝ ፋሲል ተካለልኝን ቅጥር ከሰዓታት በፊት ይፋ ያደረጉት ፈረሰኞቹ ሦስተኛ ፈራሚያቸው ታውቋል።

ከተከታታይ ሁለት የሊግ የዋንጫ የስኬት ጉዞ በኋላ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ቀዝቀዝ ብለው ሊጉን ያጠናቀቁት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ከመሾማቸው ባሻገር የመስመር አጥቂዎቹን ፍፁም ጥላሁን እና ፀጋ ከድርን አዲስ ፈራሚያቸው ማደረጋቸውን አስቀድመን መግለፃችን ይታወሳል።


ክለቡ ይፋ ያደረገው ሦስተኛ ፈረሚ የግራ መስመር ተከላካይ ጳውሎስ ከንቲባ መሆኑ ታውቋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በመቻል ተስፋ ቡድን የተጫወተው ዻውሎስ ያለፉትን አምስት ዓመታት ከአንደኛ ሊግ እስከ ከፍተኛ ሊግ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በግሉ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ሲጫወት ቆይቶ አሁን ማረፊያው ፈረሰኞቹ ቤት ሆኗል።