ሀዋሳ ከተማ የግብ ዘቡን አምስተኛ ፈራሚው አድርጓል

ሐይቆቹ የወቅቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ በይፋ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣዩ ዓመት ተሳትፎ ስብስባቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቢኒያም በላይ ፣ ወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ወንድማገኝ ሐይሉ እና ዮሴፍ ታረቀኝን ያስፈረሙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ የቡድኑ አምስተኛ ፈራሚ በማድረግ ስለ መቀላቀላቸው ሶከር ኢትዮጵያ ክለቡ ያደረሳት መረጃ አመላክቷል።

የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ በመሆን ያገለገለው የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ከአዳማ ከተማ ጋር ካሳለፈው ሁለት የውድድር ዓመታት በኋላ ስድስተኛ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ በሁለት ዓመት ውል ሆኗል።